1. ስድሳ ስድቱን የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋሳ ቃል፣ ምንም ስህተት የማይገኝበት ፣ እምነትን እና
ተግባርን በሚመለከት ሁሉ የመጨረሻው ሥልጣን ያለው ፣ህያው እና ዛሬም የሚሰራ ፣ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡

2. በእግዚአብሔር አብ፣ በእግዚአብሔር ወልድ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ አንድ አምላክ ፣እናምናለን፡፡
3. በመፍጠር ስራ፣ ፍጥረትን በመጠበቅ ፣ በመገለጥ ፣በመዋጀት እና በመጨረሻው ፍርድ የእግዚአብሔርን ፍፁም ሥልጣን እና የበላይነት እናምናለን፡፡ 4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ የተላከ መሆኑን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መፀነሱን ፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን ፣ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ፣
ለሰው ልጃች ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን ፣ መቀበሩን፣ በሶስተኛው ቀን በአካል ከሙታን መነሳቱን፣ ወደ አብ ማረጉን እና አሁንም በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ እንደሚማልድ ፣ ደግሞም በህያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በክብርና በግርማ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡

5. መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ባሕርያት ሁሉ ያሉት ፍጹም አምላክ እንደሆነ እና አምልኮ እና ስግደት እንድሚገባው እናምናለን፡፡ 6. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ በኃጥያት መውደቁን እና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡

7. ሰው ከኃጢአት ዕዳ ፣ ኃይልና ቅጣት ፣ ሊድን የሚችለው ኃጥያት የለለበት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ምትክ ሆኖ በፈጸመው የቤዛነት ስራ ብቻ በመሆኑ ኃጥያተኛ በእግዚአብሔር ፀጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሚጽድቅ እናምናል፡፡

8. ኃጥያተኛ በኃጥያቱ ተፀጽቶ ንሰሐ እንዲገባ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት እንዲሆን መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ እንሚሰራ እናምናልን፡፡

9. መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ፣ አማኙ በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ኃይልን እንደሚቀበልና በልሳን እንደምናገር በየጊዜውም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላ እናምናለን፡፡

10. መንፈስ ቅዱስ ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ለአማኞች ልዩ ልዩ የጸጋ ስጦታዎችን በማካፈል፣ድውዮችን በመፈወስ ፣ አጋንትን በማውጣትና ፣እና ተዐምራትን በማድረግ እንመድሰራ እናምናለን፡፡

11. ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተሰጣትን የታላቁን ተልዕኮ አደራ በመወጣት ወንጌልን ለሰዎች ሁሉ እንድትሰብክ እና አማኞች ደቀ መዛሙርት በማድረግ ለክርስቶስ አካል መታነጽ አስፈላጊውን ሁሉ መፈጸም እንደምትችል መንፈስ ቅዱስም ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ ወንጌል ሰባኪዎችን ፣እረኞችን እና አስተማሪዎችን እንዲሁም ሌሎች የአገልግሎት ስጦታዎችን እንደሚሰጥ እናምናለን፡፡

12. ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም የተወለዱ ሁሉ በሚገኙባት፣ የክርስቶስ አካል በሆነች፣ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ 13. ጌታችን እና መድኅንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰረት ፣ዳግም የተወለደ አማኝ ከክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ጋር መተባበሩን እንዲሁም ለኃጥያት መሞቱን እና ለጽድቅ መነሳቱን ለመግለጽ በአብ፣ በወልድ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ ውስጥ በመጥለቅ እንዲጠመቅ እንዲሁም ጌታ ዳግም እስኪመጣ ሞቱን ለመናገርና ፣ ከጌታ እና ለአማኞች ጋር ያለውን ኅብረት
ለመግለጽ የጌታ እራት እንደሚካፈል እናምናለን፡፡

14. በሙታን ትንሳኤ፣ በኃጥያተኞች ላይ በሚደርሰው የዘላለም ፍርድና አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ህይወት እናምናለን፡፡

wpChatIcon
Scroll to Top